ወደ ይዘት ይዝለሉት

ተልእኳችን፣ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ኢየሱስ የሚመራ አንድ ወጥ ታሪክ አድርገው እንዲያነብቡት መርዳት ነው።

ቪዲዮዎች

የመጽሐፍ ቅዱስን ዋና ዋና ጭብጦችና መጻሕፍት የሚያጠኑ አኒሜሽን ቪዲዮዎቻችንን ይመልከቱ፣ ያውርዱ።

ስለ BibleProject

የBibleProject ቡድንን የሚያሳይ የፎቶ ስብስብ፦ የሠራተኞች ስብሰባ፣ ሥዕል የሚስል አርቲስት፣ የቪዲዮ ቀረጻ ቦታ፣ እና መስራቾቹ ቲም ማኪ እና ጆን ኮሊንስ።

BibleProject በአሜሪካ የሚገኝ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመና በሕዝብ የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ኢየሱስ የሚመራ አንድ ወጥ ታሪክ አድርገው እንዲያነብቡ የሚረዱ ዝግጅቶችን እናቀርባለን። ግባችን ውስብስብ የሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዐሳቦችን ግልጽ በማድረግ፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ለማወቅ ለሚሹ ሁሉ ተደራሽ ማድረግ ነው። እያንዳንዱን ዝግጅት የምናደርገው፣ ዓለም ዐቀፍ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን በአእምሯችን ይዘን ነው። ምንም እንኳ ምሁራኖቻችን ከተለያዩ ክርስቲያናዊ አመለካከቶች የመጡ ቢሆኑም፣ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንደ አንድ ወጥ ታሪክ አድርገው እንዲያነብቡ ለማድረግ በአንድነትና በቁርጠኝነት የሚሠሩ ናቸው።

የአገልግሎታችን ታሪክ የጀመረው፣ የረጅም ዘመን ጓደኛማቾች የሆኑት ዶ/ር ቲም ማኪ እና ጆን ኮሊንስ እ.አ.አ. በ2014 ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲረዱ ለመርዳት፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዐሳቦችን ሥዕላዊ የአተራረክ ዘዴን በማጣመር የእንግሊዝኛ ቪዲዮዎችን በነጻ ለተመልካች ሲያቀርቡ ነበር። BibleProject በአሁኑ ጊዜ ከ140 በላይ ሠራተኞችን የያዘ ትልቅ ተቋም ሲሆን፣ በአሜሪካውያን እና በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ታግዞ፣ ከ50 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች በሺሕዎች የሚቈጠሩ ቪዲዮዎችን ለዕይታ አቅርቧል። መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንደምንረዳው የበለጠ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ፣ ይህን ሊንክ ይጫኑ።

ዝግጅቶቻችን በሙሉ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት በነጻ የምናውለው፣ እንደ ርስዎ ባሉ ለጋስ አጋዦቻችን የገንዘብ ድጋፍ ምክንያት ነው።

ባይብል ፕሮጀክትን ይቀላቀሉ

ዝግጅቶቻችን በሙሉ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት በነጻ የምናውለው፣ እንደ ርስዎ ባሉ ለጋስ አጋዦቻችን የገንዘብ ድጋፍ ምክንያት ነው።